=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
=<({አል-ቁርአን 2:153})>=
«እናንተ ያመናችሁ ሆይ በመታገስ እና በሶላት ተረዱ፤»
ፍርሃት ሲያካብብህ ሀዘን ሲያንዣብብህ እና ትካዜ ሊያስርህ ሲሻ ወዲያውኑ ወደ ሶላት ተነሳ ነፍስህ ትረጋጋለች ፤ ውስጥህም ሰላም ያገኛል። ሶላት በአሏህ ፈቃድ የሀዘንና የጭንቀት ባህርን የመቅዘፍ እንዲሁም ትካዜን የማባረር ኃይል አላት። ነብዩም (ሰ.ዐ.ወ) አንድ ጉዳይ ሲያስጨንቃቸው «ቢላል ሆይ በሶላት አሳርፈን» ይሉ ነበር። የዓይን ማረፊያቸውና የደስታ ምንጫቸውም ነበረች። በተለያዩ የታሪክ ማህደሮችም ችግሮች ሲያጋጥሟቸው እና ጉዳዩች አልፈፅም ብለዋቸው መላ ሲያጡ ኹሹዕ ያላትን ሶላት ሰግደው ኃይላቸው ተመልሶላቸው ፣ ጉዳያቸው ተፈፅሞ ፣ ወኔያቸውም የሚመለስላቸው ሰዎች እንደነበሩ አንብቤያለሁ። ጭንቅላቶች ተቆርጠው በሚበሩባቸው ፣ ነፍሶችም በሰይፍ ከአካላት የሚለዩባቸው የጦርነት ጊዜያት ፅናት ይኖርዘንድ እና እርጋታ ይሰፍን ዘንድም ሰላተል ኸውፍ ተደነገገ።
መንፈሳዊ በሽታዎች የወረሩት ይህ ትውልድ ከመስጅዶች ጋር መተዋወቅ አለበት ፤ ጌታውን ለማስደሰትና ከሚሳቀቅበት መሪር ስቃይ ለመላቀቅም ግንባሩን መሬት ላይ መድፋት አለበት። አለበለዚያ እንባዎች ዓይኑን ሲያቃጥሉት ይኖራል። ሀዘንም ህዋሶቹን ይንድበታል። ከሶላት ውጭ ሰላምና መረጋጋትን ሊሰጠው የሚችል ኃይልም አያገኝም። መገንዘብ የምንችል ብንሆን በየቀኑ የምንሰግዳቸው አምስቱ ሶላቶች እጅግ ከፍተኛ ከሆኑ ፀጋዎች ውስጥ እንደሚቆጠሩ እንገነዘብ ነበር። ምክኒያቱም ወንጀሎቻችን እንዲታበሱ ምክኒያት ናቸውና ፤ ጌታችን ዘንድ ደረጃችን ከፍ እንዲል ፤ ለጭንቀታችን እና ለበሽታዎቻችን ታላቅ ፈውስ ናቸው። ልቦናችን ውስጥ መረጋጋትን ያፈሱባቸዋል ፤ አካሎቻችንንም በደስታ ይሞሏቸዋል። እነዚያ መስጅዶችን ርቀው ሶላትን የተዉ ሰዎች ግን ከጭንቀት ከሐዘንና ከጥበት ውስጥ ይዋኛሉ።
=<({አልቁርአን 47:8})>=
«ለነሱ ጥፋት ተገባቸው ፤ ሥራዎቻቸውንም አጠፋባቸው።»
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ |
---|